ዳማሲን የማዓዛና ዘይቶች ቅመማ ቅመም ማምረቻና ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
ቦንጋ፣ ዳማሲን የማዓዛና ዘይቶች ቅመማ ቅመም ማምረቻና ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በካፋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል በጊምቦ 18 ቀበሌዎች፣ ዴቻ 4 ቀበሌዎችና ጨና ወረዳ 9 ቀበሌዎች በ5 ዓመት ውስጥ ለ5000 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ግብ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለ ማህበር ሲሆን በአንድ ዓመቱ ለ2000 ሴቶችን በማሳተፍ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን/ ዝንጅብል፣ ጦስኝ፣ እርድ፣ ኮሰረት ፣ ጤና አዳም/ እንዲሁም ሌሎች እንዲያመርቱ በማድረግ ያመረቱት ምርት ለገቢያ እንዲቀርብና የገበያ ትስስር ማህበሩ እየፈጠረላቸው መሆኑን ስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ራሄል ህሩይ ገልጸዋል::
በግንዛቤ ማስጨበጫ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም በስልጠናው በርካታ ግብዓትና ዕውቀት ያገኙ በመሆናቸው ከማህበሩ ጎን በመሆንና በቅንጅት በመስራት የህብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገልፀዋል::
ዘገባው፣ የካፋ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው